በደቡብ ክልል ህገወጥ ተግባር ፈጽመዋል የተባሉ ከ29 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ህገወጥ ተግባር ፈጽመዋል የተባሉ ከ29 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ÷ የንግድ ስራዓቱን ለማዘመንና የሸማቾችን መብት ለማስከበር የሚያስችል የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሃላፊ ማሄ ቦዳ ÷ የሸማቾችን መብት ማስጠበቅ የሁላችንም ግዴታ ሊሆን ይገባል ብለው የተወሰደው ህጋዊ እርምጃም የዚህ አንዱ አካል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ መዋቅሮች በየአካባቢው ያለውን የዋጋ ንረት ለመከላከል ትልቅ ሚና መጫወት እንዳለባቸው ም የቢሮው ሃላፊ ገልፀዋል፡፡
አላስፈላጊ ጥቅም ለማግኘት በሚሯሯጡ ስግብግብ ነጋዴዎች አማካኝነት በሚፈጠረው የምርት ጥራት ማነስ በማኅበረሰቡ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያስከትል ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የማያዳግም እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባና በማጋለጡ ሁሉም ሃላፊነት እንዳላበት አሳስበዋል፡፡
በበክልሉ በህገ-ወጥ ሥራ ላይ የተሰማሩ ከ29 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸውም አቶ ማሄ ገልጸዋል፡፡
በታሪክነሽ ሴታ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን