Fana: At a Speed of Life!

ለአገው የፈረሰኞች ማኅበር 82ኛ ዓመት በዓል የተዘጋጀው የፓናል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ የሚከበረውን የአገው የፈረሰኞች ማኅበር 82ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የፓናል ውይይት በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ።
በውይይቱ ከፌዴራል፣ ከክልል እና ከዞኑ አስተዳደር የክብር እንግዶች፣ የሀገር ሽማግሌዎና ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ የእንኳን ደህና መጣችሁ የመክፈቻ ንግግር ነው የውይይቱ መርሀ ግብር የተጀመረው፡፡
በመርሀ ግብሩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት የተካሄደ መሆኑን ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ታሪካዊ ፣ ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ ዳራ ያለው በየዓመቱ ጥር 23 የሚከበረው የአገው ፈረሰኞች ማህበር ክብረ በዓል እና የፈረስ ፌስቲቫል ነገ ለ82ኛ ጊዜ በደመቀ ሁኔታ እንደሚከበር ተገልጿል።
የአገው ፈረሰኞች የነፃነት ተጋድሎ ያስመሰከሩና በዓድዋ ጦርነትም ጀግንነታቸውን ያሳዩ መሆናቸው እና ማህበሩ የተመሰረተውም ለዚሁ መታሰቢያነት መሆኑ ይነገራል።
ፈረስ ለአዊ የእርሻ፣ የመጓጓዣ፣ የታመመን ሆስፒታል ማድረሻ፣ ከአጠቃላይ የማህበረሰቡ እንቅስቃሴ ጋር የተቆራኘ መሆኑም ተመላክቷል።
በአዊ ዞን ባሉ 9 ወረዳዎች 59 ሺህ 300 የአገው ፈረሰኞች ማህበር አባል የሚገኙ ሲሆን÷ ማህበሩ በልማት ሥራዎች ከሚያደርገው ተሳትፎ በተጨማሪ፥ የተጣላን የሚያስታርቅ ፣ በከተማው የሚያጋጥሙ ህገወጥ ተግባራትን በመቅረፍ ረገድም ከመንግስት ጋር የሚሰራ መሆኑ ታውቋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.