በመኸር ከተዘራው ሰብል ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ተሰብስቧል
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013/14 መኽር ከተዘራው ሰብል ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው መሰብሰቡን ግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።
የሚኒስቴሩ የግብርና ኤክስቴንሽን ዳይሬክተር ጀኔራል ገርማሜ ጋሩማ ለኢዜአ እንደገለጹት በ12 ነጥብ 9 ሚሊየን ሄክታር መሬት ከተዘራው ሰብል በ11 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ የደረሰ ሰብል ተሰብስቧል።
በመኽሩ ዘግይተው ከተዘሩ ጥቂት የጥራጥሬ ሰብሎች በቀር አብዛኛው እህል መሰብሰቡንና የቀረው ሰብልም በተያዘው ወር መጨረሻ እንደሚሰበሰብ ተናግረዋል።
በተያዘው ዓመት ምርቱን ለመሰብሰብ በርካታ ማሽነሪዎች ጥቅም ላይ መዋላቸውን ጠቅሰው ከ1 ሺህ 400 በላይ ኮምባይነሮች በምርት ስብሰባው ላይ መሳተፋቸውን ለአብነት አንስተዋል።
አሁንም አርሶ አደሮች በምርት አሰባሰብና ማከማቸት ወቅት የሚደርሰውን ብክነት መከላከልና ከፍተኛ ጥንቃቄም ማድረግ እንዳለባቸውም ዳይሬክተር ጄኔራሉ አሳስበዋል።
ምርት በጎተራ በሚከማችበት ወቅት በሚከሰት ንቅዘት ብክነት ስለሚደርስ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!