Fana: At a Speed of Life!

ለተፈናቀሉ ወገኖችና ለወደሙ ተቋማት ከ110 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሃት ፈጽሞት በነበረው ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎቸና ውድመት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት ከ110 ሚሊየን ብር ባላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጉን የሰዎች ለሰዎች ግብረሰናይ ድርጅት አስታወቀ።
በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ተፈጽሞባቸው የነበሩት አካባቢዎች ነጻ እንደወጡ ድርጅቱ የድጋፍ ስራዎችን ማከናወን መጀመሩን የድርጅት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ቶሎሳ ተናግረዋል፡፡
በደብረ ብርሃንና ደሴ ከተሞች በትምህርት ቤትና የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ለነበሩ ወገኖች የእለት ደራሽ እህል፣ የህጻናት አልሚ ምግብ፣ ለመልሶ መቋቋሚያ የሚውል ቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎች ተደርገጓልም ነው የተባለው፡፡
በተመሳሳይ በአፋር ጭፍራ ተፈናቅለው ለሚገኙ ከ40 ሺህ በላይ ወገኖች ድጋፍ መደረጉም ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ በሁለቱም ክልሎች ከ50 ሺህ 500 በላይ ዜጎች የአስቸኳይና ሌሎች ድጋፎች እንደተደረገላቸው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ገልጸዋል።
በክልሎቹ በተደረገው ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍ ከ85 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጓልም ነው ያሉት።
በሌላ በኩል ከመራቤቴ እስከ ወልዲያ ድረስ ባሉ ስፍራዎች ውድመት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ መደረጉን አክለዋል።
በቀጣይ መንግስት ቅድሚያ ያስፈልጋቸዋል ብሎ በለያቸው አካባቢዎችና የድጋፍ አይነቶች መነሻነት ድርጅቱ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚንቀሳቀስ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በሌላ በኩል በአሸባሪው ወራሪ ቡድን ዘረፋና ውድመት ለደረሰባቸው በደቡብ ወሎ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ለሚገኙ ዘጠኝ የጤና ተቋማት በሰሜን አሜሪካ የወሎ መረዳጃ ማኅበር ከተለያዩ ማኅበራት ገንዘብ በማሰባሰብ ከ2 ነጥብ 6 ሚልየን ብር በላይ የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት በሰሜን አሜሪካ የወሎ መረዳጃ ማኅበር ኮሚቴ አባል እና የድጋፉ አስተባባሪ አርቲስት ፀሐይ ካሳ፥ ከዚህም በፊት ማኅበራቸው የተለያየ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ሃይማኖት አየለ ድጋፉን ተረክበዋል፡፡ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ዶክተር ሃይማኖት ሌሎች አካላትም ለጤና ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.