Fana: At a Speed of Life!

ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚዘጉ የመዲናይቱ መንገዶች እና ተለዋጭ መስመሮች ይፋ ተደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚዘጉ የመዲናይቱ መንገዶች እና ተለዋጭ መስመሮች ይፋ ማድረጉን የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ፡፡
በዚሁ መሠረትም  ከአዋሬ በጥይት ቤት ወደ ፓርላማ እንዲሁም ከቡልጋሪያ ወደ አፍሪካ ህብረት የሚወስዱ መንገዶች በሁለቱም አቅጣጫ የስብሰባው ተካፋዮች ጠዋት ለስብሰባ ፣ ለምሳና ከሰዓት በኋላ ከስብሰባ ሲወጡ እነዚህ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
እንግዶቹ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በአጀብ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ለእንግዶች ቅድሚያ በመስጠት፤ ለአጀብ ስራ መንገድ ሲዘጋ ለተሽከርካሪ ክፍት እስከሚሆን ድረስ አሽከርካሪዎች በትዕግስት በመጠበቅ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያርጉ የፀጥታ ና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ጉባኤው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፡-
• ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚ/ር – መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ – ኦምሎፒያ – ወሎ ሰፈር – ጃፓን ኤምባሲ -ፍሬንድ ሺፕ -ቦሌ ቀለበት መንገድ -ኤርፖርት
• ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር -በብሄራዊ ቤተ – መንግስት -በፍልውሃ – በብሄራዊ ቲያትር- ሜክሲኮ አደባባይ – አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ፡-
• ከፓርላማ መብራት -ብሔራዊ ቤተ-መንግስት – ወዳጅነት ፓርክ – ንግድ ማተሚያ ቤት – ሞናርክ ሆቴል-ቴዎድሮስ አደባባይ-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል- ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን- ብሔራዊ ቴአትር -ሜክሲኮ አደባባይ – አፍሪካ ህብረት
• ከፓርላማ መብራት-በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን-ፍልውሃና አምባሳደር ቲያአትር ዙሪያውን ፦
• ከንግድ ም/ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ-አፍሪካ ህብረት ዋናው በር-ሳርቤት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከዓርብ ጥር 27 ቀን / 2014 ዓ/ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስከ ሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል፡፡
• ከጦር ሃይሎች – ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ፦
• በኮካ-ኮላ ድልድይ – በአብነት ተ/ኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር- ጎማ ቁጠባ
• ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ፡-ሳር ቤት-ካርል አደባባይ – በልደታ አድርገው ወደ መርካቶ እና ጎማ ቁጠባ
• የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች፦
• በአትላስ – ዘሪሁን ህንፃ- ሲግናል
• ቀለበት መንገድ – ቦሌ ሚካኤል-ሃኪም ማሞ – ወደ ጎተራ
• ቀለበት መንገድ – መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ – እንግሊዝ ኤምባሲ
• ቀለበት መንገድ -መገናኛ – አድዋ ጎዳና – አዋሬ – ቤልኤር
• በፍላሚንጎ ደንበል ጀርባ መስቀል ፍላወር መጠቀም እንደሚቻል የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይል ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ይሁን አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥመው ጥቆማ ለመስጠት በመደበኛ ስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11፣ 011-5-52-63-03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78፣ 011-5-54-36-81እንዲሁም 987፣ 991 እና 916 ነፃ የስልክ መስመሮችን መጠቀም እንደሚችል ግብረ – ኃይሉ አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.