Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቦረና ዞን ያለውን የድርቅ አደጋ ሁኔታ ለመመልከት ቦረና ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያለውን የድርቅ አደጋ ሁኔታ ለመመልከት ቦረና ገብተዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ቦረና ገብተዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው የልዑካን ቡድን የድርቅ አደጋ ጉዳት ያደረሰባቸውን የተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት የሚያስችል አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በአልአዛር ታደለ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.