በኦሮሚያ የበልግ እና ሁለተኛው ዙር የመስኖ እርሻ ልማት ሥራ ተጀመረ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የበልግ እና የሁለተኛው ዙር የመስኖ እርሻ ልማት ሥራ ተጀምሯል፡፡
ሥራው በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ አበራ ወርቁ በተመራው ልዑክ በዛሬው ዕለት በባሌ ዞን ሲናና ወረዳ በይፋ መጀመሩ የተበሰረ ሲሆን 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለማልማት መታቀዱ ተገልጿል፡፡
እንደ ክልል 353 ሺህ የሚሆን ሄክታር መሬት ላይ ስንዴን ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም ሃላፊው አመላክተዋል፡፡
በዛሬ ዕለትም ልዑካን ቡድኑ በባሌ ዞን ሲናና ወረዳ፣ ሰልቃ ቀበሌ 2 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የበልግ እርሻ ሥራ አስጀምሯል፡፡
የባሌ ዞን ግብርና ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አሊይ መሃመድ ÷ በዞኑ በበልግ እርሻ ሥራና በሁለተኛው ዙር የመስኖ ልማት 150 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ በክላስተር እንደሚለማ ተናግረዋል፡፡
በአዲስ ታምራት