ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ከአውሮፓ ሕብረት የሰብአዊ መብቶች ልዩ ተወካይ ኢሞን ጊልሞር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከአውሮፓ ሕብረት የሰብአዊ መብቶች ልዩ ተወካይ ኢሞን ጊልሞር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታና ተጠያቂነት ላይ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም በሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦት እና በሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃትና ብሔራዊ ምክክር ላይ መወያየታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡