ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የተመድ ሴቶች የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር በፕሮጀክት ሰነድ ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሴቶች የኢትዮጵያ ተወካይ አና ሙታቫቲ በሁለቱ ተቋማት መካከል በቀረበው የአራት ዓመት የፕሮጀክት ሰነድ ላይ ተወያዩ፡፡
ፕሮጀክቱ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ማጎልበት፣ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ለመከላከል፣ የሴቶች እና ልጃገረዶች የሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ ምላሽ መስጠት፣ ሴቶች በአመራር፣ በማስተባበር እና በስርዓተ ጾታ ያላቸው ተሳትፎ ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በዚህም ሚኒስቴሩ እና የተባበሩት መንግስታት ሴቶች የፕሮጀክት ሰነዱን አጠናቀው ስምምነት ለመፈራረምና ወደተግባር ለመሸጋገር መስማማታቸው ነው የተመላከተው፡፡
በተጨማሪም በፕሮጀክት ሰነዱ ላይ ተመስርተው ከተለያዩ ለጋሾች ሃብት ለማሰባሰብ በጋራ መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።