Fana: At a Speed of Life!

በልደታ ክ/ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የG+11 የመኖሪያ ቤት ግንበታ በጥራትና በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በልደታ ክፍ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የG+11 የመኖሪያ ቤት ግንባታ በተቀመጠለት ጊዜ በጥራትና በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ  ከንቲባ  አዳነች አቤቤ ግንባታው የደረሰበትን ደረጃ ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡

ከንቲባዋ ለግንባታው መጀመር የመሰረት ድንጋይ ከጣሉነት ጊዜ ጀምሮ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በየወቅቱ በልዩ ሁኔታ ክትትልና ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙም ተጠቁሟል፡፡

የህንፃው ብዛት አራት ባለ 11 ወለል ሲሆን እያንዳንዳቸው 11 ፎቆች የሚኖሩት መሆኑ ተመላክቶ  ከተጀመረ 29 ቀናትን  አስቆጥሯል፡፡

ካለምንም እረፍት ግንባታው እየተከናወነ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥  ለግንባታውም ዘመናዊ ቴክኖሎጅ አገልግሎት ላይ ውሏል ነው የተባለው።

ህንፃው ሲጠናቀቅ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን የቤት ችግር ያቃልላል መባሉን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

በተመሳሳይ ከንቲባ አዳነች÷ ከተማዋንየቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተጀመረውን የማስዋብ እና አረንጓዴ የማልበስ እንቅስቃሴ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች የሚሰሩ ቤቶች ያሉበትን ደረጃ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተመልክተዋል፡፡
የቤት ግንባታ ስራዎች በታቀደላቸው ፍጥነትና ጥራት እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመው÷ መበረታታት ያለባቸውን ጉዳዮች በመቀመር ለሌሎች ክፍለ ከተሞች ማስፋፋት እንዲቻል እንዲሁም የክረምቱን አረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴ በተደራጀ መንገድ እንዲጀመር የሚያስችል አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.