Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2014 ዓ.ም 10 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ብድር መስጠቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 10 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ብድር መስጠቱን ገለጸ።
የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው እንደገለጹት÷ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተለይም በሪፎርም ሥራዎች ላይ በስፋት ሲሠራ መቆየቱን ገልጸዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባንኩ 19 ቢሊየን ብር ብድር የማጽደቅ ዕቅድ ይዞ የነበረ ቢሆንም÷ ከዕቅዱ በላይ ማጽደቅ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በ2013 በጀት ዓመት ባንኩ ጥራት ላይ በማተኮር መሥራቱ ለተጠናቀቀው በጀት ዓመት መሰረት የጣለ አሠራር መዘርጋቱንም ነው የተናገሩት።
በ2014 በጀት ዓመት ከፈቀደው 22 ቢሊየን ብር ብድር 10 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ለተበዳሪዎች መስጠቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የባንኩ የአሠራር ማሻሻያ በደንበኞች ዘንድ እምነት በመፍጠር እና በቅርበት በመሥራት ውጤታማ መሆኑን አስታውሰው÷ በ2015 በጀት ዓመትም አሠራሩን ይበልጥ በማዘመንና በማሻሻል የሚሰጠውን ብድር 30 ቢሊየን በማድረስ ለማፅደቅ ማቀዱን ነው የገለጹት፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.