የጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴርና በሥሩ የሚገኙ ተጠሪ ተቋማት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ መርሐ ግብርን አስጀምረዋል፡፡
የቤት እድሳቱን ያስጀመሩት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ሲሆኑ÷ በመርሐ ግብሩ ላይ ሚኒስትር ዴታዎች እና የተጠሪ ተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሐ ግብር የተጀመረው÷ በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ነው፡፡
ጤና ሚኒስቴርና በሥሩ የሚገኙ 12 ተጠሪ ተቋማት በዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐግብር÷ የ12 አቅመ ደካሞችን ቤት እንደሚገነቡ ተገልጿል።
በ2014 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር የጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ የ16 አቅመ ደካሞችን ቤት ገንብተው ማስረከባቸውን አስታውሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!