ዶክተር መሳይ ሃይሉ ከዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሃይሉ ከዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ቦውሬማ ሳምቦ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በዓለም ጤና ድርጅት መካከል ያለውን አጋርነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ዶክተር መሳይ የዓለም ጤና ድርጅት በቴክኒክ ፣ በፋይናንስ እና በተለያዩ የህክምና ግብዓቶች ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ እና እገዛ አድንቀዋል፡፡
ዶክተር ቦውሬይማ በበኩላቸው÷ የዓለም ጤና ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
በተለይም ለማህበረሰቡ ስጋት ለሆኑ የኮሮና ቫይረስ ፣ የዝንጀሮ ፈንጣጣ እና መሰል በሽታዎችን ለመከላከል አስፈላጊው እገዛ እንደሚደረግ መናገራቸውን ከዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!