ለብልጽግና የተደረገው ድጋፍ ህብረተሰቡ የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ተቀብሎ ከጎኑ እንደሚሰለፍ ዳግም ያረጋገጠበት መሆኑን ፓርቲው ገለፀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለብልጽግና ፓርቲ ትናንት ምሽት የተደረገው ድጋፍ ህብረተሰቡ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና የማሸጋገር ጉዞን ተቀብሎ ከፓርቲው ጎን እንደሚሰለፍ ዳግም ያረጋገጠበት መሆኑን ፓርቲው ገለፀ፡፡
የፓርቲው የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ዛሬ ድጋፍ ለበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርቧል፡፡
1 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በተሰበሰበበት መርሃ ግብር አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች ወጣቶች እና ባለሃብቶች በበጎ ፈቃድ መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡
ድጋፉ በህብር ወደ ብልጽግና በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የፓርቲ እና የመንግስትን ሃብት ለይቶ የመጠቀም ሂደት አንዱ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡
ከተሰበበሰበው ገቢ ውስጥ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን በጥሬ ገንዘብ የተለገሰ ሲሆን፥ 2 ሺህ 600 እንስሳትም ተበርክተዋል፡፡
የትናንቱ ገቢ ማሳበባሰቢ መርሃ ግብር መጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን፥ በሶስት ምዕራፍ የሚከናወን እንደሆነም ተገልጿል፡፡
በአላዛር ታደለ