Fana: At a Speed of Life!

የሳይበር ደህንነት “ሰመር ካምፕ” ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር ያዘጋጀው የሳይበር ደህንነት “ሰመር ካምፕ” የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ፣  የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደረጄ እንግዳ  እና ሌሎች  እንግዶች ተገኝተዋል።

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ኢትዮጵያን የሚገነቡት የዛሬ ታዳጊ ወጣቶች መሆናቸውን ጠቅሰው÷ ለዚህም ወጣቶች መነሻቸውን  ኢትዮጵያ መዳረሻቸውን ደግሞ ዓለም አድርገው ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በዓለም መድረክ ከፊት የሚገኙት ሀገራት የእድገታቸው ሚስጢር በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በሳይበር ኢንደስትሪ ላይ ትኩረት አድርገው በመስራታቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርም ይሄንን መልካም ጅማሮ ለመደገፍ እና በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ነው ያረጋገጡት፡፡

አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸዉ÷ አስተዳደሩ በኢትዮጵያ በሳይበር ደህንነት የሚገኙ “ልዩ ተሰጥኦዎችን” ለማልማት የሚያስችል ማዕከል አደራጅቶ ሥራውን በጀመረ በአንድ ዓመት ብቻ 120 ሰልጣኞችን መቀበሉን ጠቁመዋል፡

በሳይበር ደህንነት የሰመር ካምፕ መርሐ ግብር የሚሳተፉ ሰልጣኞች ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 23 እንደሆኑ እና 60 ባለ ልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች ተሳታፊ መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.