Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ የ2014 ሪፖርት እና የ2015 በጀት አመት እቅድ ገለጻ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የ2014 በጀት አመት ሪፖርት እና የ2015 በጀት አመት እቅድ ገለጻ ዛሬ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ÷ ፓርቲውን ጊዜውን ሊመጥን በሚችል ሁኔታ ለማደራጀት እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

በተለይም ከሕዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ የሚችል፣ ለውጥን በአግባቡ ማስቀጠል እና ብልፅግናዊ ትልሞችን የማሳካት አቅም ያለው አመራርን ከመፍጠር አኳያ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ፖሊሲዎቹ እና ስትራቴጂዎቹ ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካን ችግሮች መፍታት በሚችል ማዕቀፍ መቃኘት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

የአረንጓዴ ዓሻራን ተልዕኮ ማስፈፀም፣ የህዳሴ ግድብ ተሳትፎ እንዲሁም የፓርቲውን 1ኛ ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ ማካሄድን የመሰሉ በንቅናቄ የሚሰሩ ተግባራትን በማስፈፀም ደረጃ የተገኙ ውጤቶች አበረታች ናቸውም ብለዋል፡፡

የአመራሮችን ብቃት ማሳደግ፣ በብልሹ አሰራር ውስጥ ተዘፍቀው የተገኙትን ማጥራት እና ተጠያቂነት ማስፈን ቀጣይ የፓርቲው የቤት ስራ ይሆናልም ነው ያሉት፡፡

በውይይቱ ላይ በርካታ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተው ለቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ተልዕኮ ተቀብለዋል መባሉን ከብልፅግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.