አሸባሪው ህወሓት ዳግም ወደ ግጭት መግባቱ ከጦርነት አባዜው አለመላቀቁን ያሳያል – ምሁራን
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን የአፍሪካ ህብረትን አደራዳሪነትና የሰላም ጥሪን አልቀበልም ብሎ እንደገና ወደ ግጭት መግባቱ ጦርነት ናፋቂነቱን ያረጋግጣል ሲሉ ምሁራን ገለጹ፡፡
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጥናት ምሁር ንጋቱ አበበ÷ ቡድኑ እንደገና ዛሬ የጀመረው ጦርነት ፀብ ጫሪነቱን፣ እብሪተኝነቱንና የባዕዳን ጉዳይ አስፈፃሚ ኃይል መሆኑን አረጋግጧል ብለዋል።
መንግስት ለአፍሪካ ችግሮች የአፍሪካ መፍትሔ መርህን ለመተግበር የሰላም ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የገለጹት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት መምህሩ ሱራፌል ጌታሁን በበኩላቸው÷ ህወሓት የሰላም ውይይቱን ጥረት ሲያደናቅፍ መቆየቱንም ነው የጠቆሙት፡፡
የቡድኑ ህልውና ግጭት መፍጠር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ከግጭት ትንኮሳውና ከጦርነት አባዜው ዛሬም አለመቆጠቡን ነው ምሁራኑ ያስረዱት፡፡
የሽብር ቡድኑን ትክክለኛ አቋምና አሳሳች መልክ ለዓአለም አቀፉ ማህበረሰብና ለአፍሪካውያን ለማስረዳት መንግስት ትኩረት መስጠት እንዳለበትም ምሁራኑ ጠቁመዋል፡፡
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!