የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመረውን ሥራ እደግፋለሁ- ካናዳ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የካናዳ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፍ ገለፀ፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ከካናዳ አምባሳደር ስቴፋኒ ጆቢን ጋር ባደረጉት ውይይት÷ በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ላይ መክረዋል፡፡
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ መርሐ ግብርን ተግባራዊ ለማድረግ የካናዳ መንግስት ሊያደርግ ስለሚችለው ድጋፍ እና የበጎ ፈቃደኞች መምህራን ስምሪት ላይ መወያየታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡
አምባሳደር ስቴፋኒ ጆቢን በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመረውን እንቅስቃሴ አድንቀው የካናዳ መንግሥት ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ መርሐ ግብርሐ ግብር እንዲሳካ÷ በኤምባሲያቸው በኩል፣ በካናዳ ዓለምአቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስቴር እና በካናዳ ዩኒቨርሲቲዎች አማካይነት እንዲሁም በኦታዋ ከተቋቋመው የኢትዮጵያ ግብረኃይል ጋር በመሆን የሚጠበቅብንን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!