Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ ከዴንማርክ የስደተኞች ም/ቤት የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከዴንማርክ የስደተኞች ምክር ቤት የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ጀምስ ክርቲስን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በክልሉ በተከሰተው በድርቅ ሳቢያ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ነዋሪዎች አስፈላጊውን ሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች የክልሉ መንግስት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ አቅርቦትን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በትኩረት መወያየታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይት መድረኩ በምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ዋና ኃላፊ ሱዛን ክላርክ የተመራ የስራ ሃላፊዎች ቡድን መሳተፉ ተጠቁሟል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.