Fana: At a Speed of Life!

አሰልጣኝ ውበቱ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከሱዳን ለምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊፋ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ወቅትን በመጠቀም ከሱዳን ብሄራዊ ቡድን ጋር መስከረም 13 እና መስከረም 16 አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የወዳጅነት ጨዋታ ያከናውናል።

ለጨዋታው እንዲረዳም የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን ከኢትዮ ኪክ ኦፍ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች በነገው ዕለት ሪፖርት በማድረግ በቦሌ ጁፒተር ሆቴል ተሰባስበው ልምምድ እንደሚጀምሩም ነው የተገለጸው።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች፦

ግብ ጠባቂዎች

በረከት አማረ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ሰኢድ ሀብታሙ (አዳማ ከተማ)፣ ዳንኤል ተሾመ (ድሬዳዋ ከተማ)

ተከላካዮች

አስራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ሱሌማን ሃሚድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ሄኖክ አዱኛ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ረመዳን የሱፍ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ጊት ጋትኩት (ሲዳማ ቡና) ፣ አስቻለው ታመነ (ፋሲል ከነማ) ፣ ፍሬዘር ካሳ (ሀዲያ ሆሳእና)

አማካዮች

ጋቶች ፓኖም (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ሽመልስ በቀለ (ኤል ጉውና/ግብፅ) ፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ) ፣ በዛብህ መለዮ (ፋሲል ከነማ) ፣ ታፈሰ ሰለሞን (ፋሲል ከነማ) ፣ መሱድ መሀመድ (አዳማ ከነማ) ፣ ከነአን ማርክነህ (መቻል)

አጥቂዎች

በረከት ደስታ (መቻል) ፣ ዳዋ ሁቴሳ (አዳማ ከተማ) ፣ ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና) ፣ ቸርነት ጉግሳ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ናቸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.