Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ጋር ተወያዩ፡፡

ከአውሮፓ ፓርላማ የሴቶች መብትና የሥርዓተ ፆታ እኩልነት ኮሚቴ እንዲሁም የልማት ኮሚቴ የልዑካን ቡድንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚህ ወቅትም ለሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ ስደተኞች፣ ለስደት ተመላሾች እና አረጋውያን ሚኒስቴሩ ከማህበራዊ ጥበቃ አንጻር የሚያከናውናቸውን ተግባራት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የልኡካን ቡድኑ አባላት ስለሴቶች መብት፣ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ የሴት ልጅ ግርዛት፣ የሴቶች ትምህርት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም የስርዓተ ፆታን በተመለከተ እየሰተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጠይቀዋል።

ሚኒስትሯ በሰጡት ምላሽ በመንግስትና ሚኒስቴሩ የሴቶችን መብት ለማስጠበቅና አቅማቸውን በማጎልበት በፖሊሲ፣ በተቋማዊና በፕሮግራም ደረጃ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ጥረት በተመለከተ ማብራራታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.