Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን የቱሪዝም ሃብት የሚያስተዋውቅ ዐውደ ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን ዘርፈ ብዙ የቱሪዝም ሃብት የሚያስተዋውቅ ዐውደ ርዕይ በአሶሳ ከተማ ተከፍቷል፡፡

የኢፌዴሪ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ ሀሰን ዐውደርዕዩን መርቀው ከፍተዋል።

በአሶሳ እየተከበረ የሚገኘውን 35ኛው የዓለም ቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ ለዕይታ ክፍት በሆነው ዐውደ ርዕይ÷ በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ፣ ሰው ሠራሽ እና ታሪካዊ መገለጫዎች ለዕይታ መቅረባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎቹ የሼህ ሆጀሌ አልሃሰን የችሎት አዳራሽ፣ መካነ መቃብር እና የክልሉን ሙዚየም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ሼህ ሆጀሌ አልሃሰን ከ1817 እስከ 1931ዓ.ም ድረስ የአሶሳ ከተማ ገዥ የነበሩ ሲሆን ፥ የችሎት አዳራሻቸው በ1886 ዓ.ም የተገነባና በአሶሳ ከተማ ውስጥ የሚገኝ በቱሪስት መስህብነቱ የሚታወቅ ታሪካዊ ሥፍራ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.