ኢሬቻ የአንድነት አርማ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ ተከብሮ ተጠናቋል – አቶ ፍቃዱ ተሰማ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢሬቻ የዕርቅ፣ የወንድማማችነት፣የሰላምና የአንድነት አርማ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ ተከብሮ መጠናቀቁን በበልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ ገለጹ፡፡
አቶ ፍቃዱ በሰጡት መግለጫ፥ የኢሬቻ በዓል አንድነትና ወንድማማችነት የታየበት ሆኖ በሰላም መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡
በዓሉ ጠላት እንዳሰበው ሳይሆን የኦሮሞ ባህልና ዕሴት በጠበቀ መልኩ መከበሩንም ተናግረዋል፡፡
ኢሬቻ የኢትዮጵያውያን አንድነት መገለጫ፣ ኅብረብሔራዊ አንድነት የሚጠነክርበትና የእያንዳንዳችን ማንነትና የጋራነት ውበታችን የተረጋገጠበት ነው ብለዋል፡፡
ኢሬቻ የዕርቅ፣ የወንድማማችነት እንዲሁም የሰላምና የአንድነት አርማ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ ተከብሮ መጠናቀቁንም ገልጸዋል፡፡
በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ላበረከቱ÷ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች፣ ቄሮዎች፣ ቀሬዎች፣ ለወጣት አደረጃጀቶች፣ ለኦሮሞ ሕዝብ እና ለጸጥታ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በአያና ደሬሳ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!