የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች በግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ ዋናው ፅህፈት ቤት የተዘጋጀው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ይህንን ደጀንነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በዚህ ወቅት እንዳሉት የአሸባሪውን ህወሓት ወረራ ለመመከት እየተፋለመ ላለው መከላከያ ሰራዊት የፓርቲው አባላትና አመራሮች ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
ደም መለገስ የደጀንነት ብቸኛ መገለጫ አለመሆኑን ያነሱት አቶ አደም በቀጣይም ሰራዊቱ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ለማድረግ ብልፅግና ፓርቲ ቁርጠኛ ነው ማለታቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!