Fana: At a Speed of Life!

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በጣናና ሐዋሳ ሐይቆች አካባቢ ሆቴል ለማልማት ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በጣና እና ሐዋሳ ሐይቆች አካባቢ ሆቴል ለማልማት ከማሪዮት ኢንተርናሽናል ጋር በጋራ ተፈራረመ፡፡

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ “ፕሮቴያ ማሪዮት”ን በባህር ዳር ከተማ ጣና ሀይቅ እና በሐዋሳ ሐይቅ ደግሞ “ፎር ፖይንት ባይ ሸራተን”ን ለመክፈት የሚያስችሉ ሦስት ስምምነቶችን ነው ከማሪዮት ኢንተርናሽናል ጋር የተፈራረመው።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከማሪዮት ኢንተርናሽናል ጋር በባህር ዳር የሚገኘውን ጣና ሆቴል እና ሐዋሳ የሚገኘውን ፕሮግረስ ኢንተርናሽናል ሆቴልን በ“ፎር ፖይንት ባይ ሸራተን” ብራንድ እንዲሁም የብሉ ናይል (አቫንቲ) ሪዞርትን በ“ፕሮቴያ ማሪዮት” ብራንድ ለመክፈት ነው ስምምነቱን ያደረገው፡፡

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኩል ስምምነቱን የተፈራረሙት ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ጀማል አህመድ እና የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ሰለሞን ዘውዱ ናቸው፡፡

ከሪም ቼሎት፣ ጁጋል ኩሻላኒ እና ኤድዋርድ ኤድዋርት ደግሞ በማሪዮት በኩል ስምምነቱን መፈረማቸውን ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.