Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ የሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚዬም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያና አሜሪካ አዘጋጅነት የሚካሄደውና በአይነቱ ልዩ የሆነው የ2026 የአፍሪካ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚዬም በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ሲምፖዚዬሙ በሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ያለውን አህጉራዊ ትብብር ማጠናከር፣ ፈጠራን ማፋጠን እና የጋራ ጸጥታና ዝግጁነትን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው።

በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር)፣ የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ (አፍሪኮም) አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ተሳትፈዋል፡፡

ከ40 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የመከላከያና የሎጂስቲክስ መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ አጋሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት የወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ መሪዎችም ተገኝተዋል፡፡

ጉባዔው ተሳታፊዎች በሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ያሉ ክፍተቶችን በመለየት ዘላቂ፣ አዋጭና ተግባራዊ መፍትሔዎች ላይ ይመክራሉ።

ሲምፖዚዬሙ በአሜሪካና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የትብብር ግንኙነት በማጠናከር በአፍሪካ የመከላከያ ተቋማት መካከል የልምድ ልውውጥና የጋራ ትብብር ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሚቆየው ሲምፖዚዬም በአፍሪካ ሀገራት የመከላከያ ተቋማት መካከል የልምድ ልውውጥን ማሳደግና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችሉ ውይይቶች ይደረጋሉ።

በመሳፍንት ብርሌ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.