Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ለሥራ ዕድል ፈጠራ ለሚያደርገው ጥረት ድጋፋችን ይቀጥላል- ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ለሥራ ዕድል ፈጠራ እያደረገ ያለው ጥረት ውጤታማ በመሆኑ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሚደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ካቢኔ በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ተወያይተዋል፡፡

የክልሉ መንግሥት ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ በትኩረት እየሠራ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡

ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በተሻለ ሁኔታ ለመሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም መክረዋል፡፡

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት÷ የኦሮሚያ ክልል በሥራ እድል ፈጠራ የተሸለ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርም አስፈለጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል፡፡

የሥራ ዕድል ፈጠራን ማፋፋት እና ክህሎትን ማበረታታት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ÷ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃአመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.