Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በምሥራቅ ሸዋ ዞን በኩታ ገጠም እየለማ ያለ የበቆሎ ማሳን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በምሥራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ወረዳ በኩታ ገጠም እየለማ ያለን የበቆሎ ማሳ ጎበኘ፡፡

የምሥራቅ ሸዋ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መስፍን ተሾመ በጉብኝቱ ላይ ባደረጉት ገለጻ÷ ዛሬ ከተጎበኘው በ2 ሺህ 16 ሔክታር ላይ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል 131 ሺህ ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጌቱ ገመቹ በበኩላቸው÷ እንደክልል በ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ሔክታር ላይ በኩታ ገጠም በቆሎ እየለማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከእዚህም 67 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚገኝ ይጠበቃል ነው ያሉት።

በተመሳሳይ የልዑካን ቡድኑ አባላት በአዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ጋሎ ሂራጴ ቀበሌበ2 ሺህ ሔክታር ላይ እየለማ ያለውን የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ እንደክልል በመስኖ እና በመኸር እርሻ በ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ሔክታር ላይ ስንዴ በማልማት 100 ሚሊየን ኩንታል ሰብል ለመሰብሰብ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

ይህ የልማት ሥራ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ስንዴን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተያዘውን ዕቅድ ያግዛል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ፡፡

በዳግማዊ ዴክሲሳ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.