Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መንግስት በአፍሪካ ህብረት በኩል በሚካሄደው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በአፍሪካ ህብረት በኩል በሚካሄደው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።
 
አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ንግግሩ የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 14 ቀን በደቡብ አፍሪካ እንደሚካሄድ ማሳወቁን ጠቅሰዋል።
 
መንግስትም በዚህ የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን ነው የገለጹት።
 
ሆኖም አሁንም መንግስት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚወስደውን የመከላከል እርምጃ ለማጠልሸት፣ የሀሰት ክስን ለመሰንዘርና የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ በሚጥሩ አካላት ላይ የተሰማውን ቅሬታ ገልጸዋል።
መንግስት በአንድ በኩል ህግ በማስከበር አቋሙ በመፅናት የሚወስደው እርምጃ እንደተጠበቀ ሆኖ፥በሌላ በኩል በአፍሪካ ኅብረት አማካኝነት ለሚካሄደው የሰላም ውይይት ዝግጁ መሆኑን እንዳረጋገጠ ይታወሳል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.