Fana: At a Speed of Life!

ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ስንዴ መግዛት እንደምትፈልግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ስንዴ መግዛት እንደምትፈልግ የሀገሪቱ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የጅቡቲ ግብርና ሚኒስትር መሀመድ አሕመድ አዋሌህ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያ ለጂቡቲ በግብርናው ዘርፍ የፍራፍሬ ምርትና የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን በማመቻቸት ከፍተኛ ሚና አላት።

ኢትዮጵያም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በጀመረችው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር መሰረት÷ ለጅቡቲ ለምግብነትና ለደን ልማት የሚውሉ ችግኞችን መለገሷን ጠቅሰዋል።

ጅቡቲ ኢትዮጵያ ከጀመረችው የስንዴ ልማት ብዙ ተሞክሮ እንደምትወስድ ጠቁመው÷ ስንዴ ወደ ውጭ ገበያ ማቅረብ ስትጀምር ጅቡቲ የመግዛት ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.