ጠ/ ሚ ዐቢይ በአራዳ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የስፖርት ማዘውተሪያ መርቀው ከፈቱ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ በአዲስ መልክ የተገነባውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መርቀው ከፈቱ።
በተለምዶ “15 ሜዳ” ተብሎ የሚጠራው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፋራ ከዚህ ቀደም ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ምቹ እንዳልነበር ተጠቁሟል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አነሳሽነት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በአዲስ መልኩ ተገንበቶ በመጠናቀቁ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል ።
የስፖርት ማዘውተሪያው ግንባታ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ በሚያመች መልኩ የተገነባ በመሆኑ የቀደመ አግልግሎቶቹን እንደሚሰጥ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የስፖርት ማዘውተሪያው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመርቆ ሲከፈት ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችም ተገኝተዋል።
የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራው ግንባታ የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮጀክት አካል መሆኑም ታውቋል።