በቡና እሴት ሰንሰለት ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ብድር ማመቻቸት የሚያስችል የ10 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጀክት ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብርና ሚኒስቴር ከተመድ ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጋር በቡና እሴት ሰንሰለት ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ብድር ለማመቻቸት የሚያስችል የ10 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጀክት ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የግብርና ሚኒስትሩ ኡመር ሁሴን እና በኢትዮጵያ የተመድ ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳይሬክተር አውራሊያ ፓትሪዚያ ካላብሮ ናቸው፡፡
ስምምነቱም በቡናው እሴት ሰንሰለት የተሰማሩ ባለድርሻ አካላትን የሚያግዝ ፕሮጀክት ላይ በትብብር ለመሥራት ያለመ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
አቶ ኡመር ሁሴን በስምምነቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ለቡና ላኪዎች፣ አቅራቢዎችና አምራቾች የፋይናንስ ውስነንት ዋነኛ ማነቆ እንደነበር አስታውሰው የዛሬው የቴክኒካልና የገንዘብ ትብብር ስምምነት ችግሩን ያቃልላል ብለዋል።
አውራሊያ ፓትሪዚያ ካላብሮ በበኩላቸው ትብብሩ በቡና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለድርሻ አካላትን በመለየት ድጋፍ ለማድረግ እንደሚያግዝ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ፥ ፕሮጀክቱ የቡናን መጠን፣ ጥራት እና ዋጋን ለማሳደግ በአነስተኛ ወለድ የብድር አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አመላክተዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ለቡና አምራቾች፣ አቅራቢዎችና ላኪዎች እገዛ የሚያደርግ ሲሆን÷ ለፕሮጀክቱ የተመደበው የ10 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ የተገኘው ከጣልያን መንግስት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!