ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኮምቦልቻ ከተማ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት አምራቾችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት አምራቾችን ጎብኝተዋል።
የሀገሪቱን የኢንቨስትመንት ዐቅም ለማጉላት ያለመው ‘‘የኢትዮጵያ ታምርት’’ ዘመቻ በተጀመረ ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ በሚገኘው የወጪ ንግድ ገቢ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።