Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ መቀሌ ዳግም በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ከአዲስ አበባ መቀሌ ዳግም መደበኛ በረራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡
 
ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ተቋርጦ የነበረው የአየር ትራንስፖርት ዛሬ ቀን 6 ሰዓት ላይ በይፋ መጀመሩን የአየር መንገዱ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ አቶ አሸናፊ ዘርዓይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት
ተናግረዋል፡፡
 
የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ መቀሌ ዳግም በረራ መጀመሩ መንግስት ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋገጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
ተቋርጦ የቆየውን የአየር በረራ በሁሉም የትግራይ ክልል መዳረሻዎች ለማስጀመር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑም በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተጠቁሟል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.