Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ100ሺህ በላይ ዜጎች የማዕድ ማጋራት ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአጠቃላይ የገና በአልን ምክንያት በማድረግ ከ100ሺህ በላይ ዜጎች የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውና ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን የተለያዩ በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር በተገኘ ከ300ሚሊየን ብር፤ በላይ በሆነ ወጪ ለገና በዓል የማዕድ ማጋራት ተከናውኗል፡፡

በዚሁ ወቅት ከንቲባ አዳነች እንደተናገሩት÷ ከተማችን አዲስ አበባ የፍቅርና የመደጋገፍ ከተማ እንድትሆን በርትተን እንሰራለን  ብለዋል፡፡

በሁሉም ረገድ ከተማችን ሰላማዊ፣ንጹህና ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን የምታቅፍ እንድትሆንም በዘላቂነት ከአጋር አካላት ጋር ይሰራል ነው ያሉት።

በምናከናውናቸው የልማት ስራዎች ሁሉ ዝቅተኛ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የመደገፍ ስራ እንደሚሰራ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በሙሉ ምስጋና ማቅረባቸውን የከንቲባ  ጽህፈት ቤት መረጃ  ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.