Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ ነገ በሚያደርገው ልዩ ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያፀድቃል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባውን በነገው እለት ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብም መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የሚንስትሮች ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልጋት ከስምምነት በመድረስ ውሳኔ ማሳለፋቸው ይታወሳል።

አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቅ ስላለበት ነገ በሚኖረው 2ኛ ልዮ ስብሰባ ምክር ቤቱ የቀረበውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም ምክር ቤተ በልዩ ስብሰባው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.