በኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ሰው የኮሮናቫይረስ ተገኘበት
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ሰው የኮሮናቫይረስ እንደተገኘበት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 294 ሰዎች መካከል1 ግለሰብ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት ነው በፌስቡክ ገፃቸው የገለፁት።
በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 56 ከፍ ብሏል።
የኮሮናቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ2 ሺህ 790 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መከናወኑንም አስታውቅዋል።
በኢትዮጵያ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል አራቱ ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፤ ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው መሸኘታቸው ይታወሳል።