ቻይና ከቀጣዩ ረቡዕ ጀምሮ ከኢትዮጵያ በሚገቡ የወጪ ምርቶች ላይ ቀረጥ አነሳች
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከቀጣዩ ረቡዕ ጀምሮ ከኢትዮጵያ በሚገቡ የወጪ ምርቶች ላይ ቀረጥ ማንሳቷን አስታወቀች።
ውሳኔው ቻይና ለአፍሪካ ሀገራት ይፋ ባደረገችው “የልዩ ቀረጥ ማሻሻያ” ማዕቀፍ የሚተገበር መሆኑን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።
በዚህም ከፈረንጆቹ መጋቢት 1 ቀን ጀምሮ ወደ ቻይና ከሚላኩ የኢትዮጵያ የወጪ ምርቶች መካከል በ98 በመቶው ላይ ቀረጥ መነሳቱን ነው ያስታወቀው።
ይህን ተከትሎም 8 ሺህ 804 የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ ቻይና ከቀረጥ ነጻ የሚገቡ ይሆናል።
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በ8ኛው የአፍሪካ ቻይና የሚኒስትሮች የትብብር ፎረም ላይ፥ ቤጂንግ ከአፍሪካ ለሚገቡ የወጪ ንግድ ሸቀጦች ያደረገችውን “ልዩ የቀረጥ ማሻሻያ” ይፋ አድርገዋል።
በዚህ ወቅትም ኢትዮጵያ ወደ ቻይና ከምትልካቸው ሸቀጦች መካከል ከፈረንጆቹ መጋቢት 1 ቀን ጀምሮ 98 በመቶው በዚሁ “የልዩ ቀረጥ ማሻሻያ” ከቀረጥ ነጻ ይገባል ተብሏል።
ይህም የሀገራቱን የኢኮኖሚ ግንኙነት በማጠናከር ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያጎለብት ታምኖበታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!