የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ ተከበረ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ጉዱማሌ ተከበረ።
ትናንት በፍቼ አከባበር የጀመረው የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ ዛሬ የመጨረሻ የሆነው የጫምባላላ ስርዓት ተከብሯል፡፡
በፍቼ የመዝናናትና የማመስገን ቀን በመሆኑ የሲዳማ ተወላጆች በህብረት በመሆን በጉዱማሌ አደባባይ በዓሉን በማክበር ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የሲዳማ አባቶች የሲዳማ ባህላዊ ጭፈራ የሆነውን የቄጣላ ጨዋታን ተጫውተዋል፡፡፡፡
በዓሉ በብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃ እና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች እየተከበረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በስነ ስርዓቱ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የድቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በጥላሁን ይልማ፣ ብርሃኑ በጋሻና ተመስገን ቡልቡሎ