የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የዕውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር አከሄደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ ፖሊሶች የከፍተኛ ማዕረግ እድገት፣የዕውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር አከሄደ።
በመርሐ ግብሩ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱራህማን ፣አባገዳዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችም ታድመዋል፡፡
በመድረኩ የማዕረግ እድገት ፣የሜዳሊያ እና ሌሎቹም ሽልማቶችና እውቅናዎች ተሰጥተዋል።
የሀገርን ሠላም ለማረጋገጥ እና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ህይወታቸውን ላጡ የሰራዊት አባላት ቤተሰቦችም ምስጋና እና ዕውቅና ተበርክቷል።
በዚሁ ወቅት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንደገለጹት÷ ኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይልን መልሶ ለማደራጀት የወጣውን እቅድ ተግባራዊ በማድረግ ምሳሌነት ያለው ስራ አከናውኗል፡፡
ብቃት ያለው የፖሊስ ሃይልን ለማደራጀት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እያከናወነ የሚገኘውን ተግባር ስኬታማ ለማድረግ መከላከያ ሰራዊት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡
በይስማው አደራው