Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ተገኝተዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያዘጋጀው እና ከሚያዚያ 28 ቀን 2015 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ሲካሄድ የቆየው “ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2015” ዛሬ ይጠናቀቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አገር አቀፍ ኤክስፖውን መርቀው መክፈታቸው ይታወሳል።

በኤክስፖው ላይ 124 አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን እንዳቀረቡም ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.