Fana: At a Speed of Life!

ያመፁ የዋግነር ቅጥረኛ ወታደሮችን አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጡ ፕሬዚዳንት ፑቲን አስጠነቀቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያመፁ የዋግነር ቅጥረኛ ወታደሮችን እንደሚቀጡ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስጠነቀቁ፡

የዋግነር ቅጥረኛ ቡድን የሩሲያን ወታደራዊ አመራር ለመጣል መንቀሳቀሱን ከገለጸ ወዲህ ፕሬዚዳንት ፑቲን ለመጀመሪያ ጊዜ መግለጫ ሰጥተዋል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው የህልውና ጦርነት ላይ እንደምትገኝና ሁሉም ኃይሎች በህዝቡ ላይ የደረሰውን ክህደት እንዲያወግዝና እንዲመክት ጥሪ አቀረቡ፡፡

በመግለጫቸውም፥ ሁሉም ሃይሎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ያሳሰቡ ሲሆን፥ ድርጊቱን “ክህደት” እና ህዝባችን ከኋላ የወጋ ሴራ ነው” ሲሉም ነው ያወገዙት፡፡

በአንጻሩ የዋግነር ቡድን በደቡብ ሮስቶቭ የመከላከያ ዋና መሥሪያ ቤትን የተቆጣጠረ ሲሆን ፥ ዋግነር በሩሲያ ጦር ላይ ነፍጥ ማንሳቱ ያልተጠበቀና አስደንጋጭ ነው ሲሉም ብዙዎች እየተነጋሩ ነው፡፡

ይህን ተከትሎም የሩሲያው ፕሬዚዳንት በሰጡት መግለጫ ባመፁ የቡድኑ አባላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ዝተዋል።

የቅጥረኛው ቡድን መሪ እና መሥራች የሆኑት የቭጌኒ ፕሪጎዢን ፑቲን አሉኝ ብለው ሚስጥራቸውን ከሚያካፍሏቸው መካከል በግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነበሩ፡፡ አሁን ግን በጥብቅ የሚፈለጉ ተከሳሽ ጠላት ሆነዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ለሩሲያው መሪ በሰጡት የአጸፋ ምላሽ “የሮስቶቭ ከተማን ተቆጣጥሬያለሁ ያሉ ሲሆን ፥ ነጻ አወጣታለሁ ያሏት የሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ እገስግሳለሁና ጠብቁኝ ፤ ትከሻ እንለካካለን” ብለዋል፡፡

“በሩሲያ የተንሰራፋውን ቢሮክራሲ፣ ሙስና እና በቃል አለማደርንም አስቆማለሁ ፤ ለአይናችሁ ጤና” ብለዋል፡፡

ሆኖም ይህን ሁሉ የማቆመው የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ እኔን ለማነጋገር ካለሁበት ሲመጡ ነውም ብለዋል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በቴሌግራም ገጻቸው የሩሲያ መንግስት የእጁን ነው ያገኘው ዓይነት ኃሳብን አጋርተዋል፡፡

የክፋትን መንገድ የተከተለ ራሱኑ ያጠፋዋል ሲሉም ቃል በቃል ገልጸዋል፡፡ በዚህም የሩሲያ ደካማ ጎን ግልጽ ነውም ብለዋል፡፡

ይህም ብዙዎችን ወደጦርንት የማገደ እንደሆነ ጠቅሰው ፥ ሩሲያ አሁንም ጦሯን በዩክሬን ማሰማራቷን የማታቆም ከሆነ ከዚህ የባሰ ችግር ውስጥ ትገባለች ሲሉ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.