Fana: At a Speed of Life!

ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከዓለም ባንክ የፕሮግራሞች ገለልተኛ ግምገማ ቡድን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች ከዓለም ባንክ የፕሮግራሞች ገለልተኛ ግምገማ ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ገለልተኛ ቡድኑ ባንኩ ከ2012 እስከ 2022 በኢትዮጵያ የነበረውን ተሳትፎ የሚገመግም ሲሆን÷ ከተለያዩ ዘርፎች ጋር እንደሚገናኝም ይጠበቃል፡፡

ከግምገማው በኋላም ቀጣይ እቅዶችን በማዘጋጀት የልማት ትብብር መስኮችን እንደሚለይ ተጠቁሟል፡፡

ግምገማው ባንኩ በኢትዮጵያ የሰራቸው የልማት ትብብር ስራዎች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመሆን በዝርዝር ይገመግማል ተብሏል፡፡

ለአብነትም የአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተገናኙ ተግባራት እንዲሁም የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ የተሰሩ ስራዎች እንደሚጠቀሱ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ገለልተኛ ቡድኑ ባንኩ በኢትዮጵያ ያለውን የልማት ትብብር ተሳትፎ በተመለከተ ከፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እና ከሚኒስትር ዴኤታ ነመራ ገበየሁ (ዶ/ር) ጋር መክሯል፡፡

ከግምገማው ቀጥሎ በሚዘጋጁ እቅዶች ላይ ባንኩ የኢትዮጵያን የልማት የትኩረት መስኮችና ቅድሚ የሚሰጣቸውን ፍላጎቶች በመለየት የትብብር ማዕቀፉ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል፡፡

የባንኩ የፕሮግራሞች የግምገማ ቡድን አባላት ከተለያዩ አካላት ጋር በመገናኘት የሚወያዩ ሲሆን÷ ካለፉት 10 ዓመታት ተሞክሮዎችን በመውሰድና የቀጣይ የኢትዮጵያ የልማት መስኮች በማገናዘብ አዲስ የልማት ትብብር ማዕቀፍ ይቀርጻል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.