Fana: At a Speed of Life!

የድሬደዋ ወጣቶች የዜጎችን ማህበራዊ ችግር ለማቃለል በሚችሉት አቅም እንዲሳተፉ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬደዋ ወጣቶች በክረምቱ ወራት የዜጎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለማቃለል በሚችሉት አቅም እንዲሳተፉ የከተማው ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ጠየቁ።

“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ ከ76 ሺህ በላይ ወጣቶች የሚካፈሉበት የበጎ ፍቃድ የክረምት ስራዎች ዛሬ በድሬዳዋ ተጀመሯል።

ከ32 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የልማት ስራዎች ይከናወንበታል የተባለው የድሬዳዋ ወጣቶች የክረምት የበጎ የልማት ስራዎች በይፋ የተጀመረ ሲሆን÷ አምና ተሳተፉት የዕውቅናና የምስጋና መርሃግብር ተካሂዷል።

ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ÷ ክረምቱን ወጣቶች ለዜጎች የማህበራዊና የምጣኔ ሃብት ችግሮች መቃለል እምቅ ጉልበታቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ክህሎታቸውን እንዲጠቀሙ ጠይቀዋል።

በድሬደዋ ገጠርና ከተማ አምና በትምህርት፣ በጤና፣ በመሠረተ ልማት ዕድሳት፣ በአቅመ ደካሞች ቤት ቤት ጥገና፣ በፅዳትና ውበት፣ በትራፊክ አደጋ መከላከልና ሌሎች ዘርፎች ከ186 ሺህ 400 በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

በዚህም ከ26 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የልማት ስራዎች በመስራት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ማለታቸውን የከተማ አስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዘንድሮም የበጎ ልማት ስራዎች ላይ የሚሳተፉት ወጣቶች የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር የነዋሪዎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፊራኦል ቡልቻ በበኩላቸው ÷በክረምቱ በ13 የልማት መስኮች ከ76 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሳትፈው ግምቱ ከ32 ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ የልማት ስራዎች ያከናውናሉ ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.