ኢ/ር ታከለ ኡማ ከወሎ ሰፈር—ኡራኤል ያለውን የመንገድ ግንባታ ተመለከቱ
አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 27፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከወሎ ሰፈር—ኡራኤል እየተደረገ ያለውን የመንገድ ግንባታ ተመልክተዋል።
35 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ከወሎ ሰፈር ኡራኤል እየተገነባ ያለው መንገድ 1ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በአንድ ጊዜ 6 የተሽከርካሪዎችን ማጓጓዝ የሚያስችል ነው ተብሏል።
ከመንገድ ግንባታው ጋር በተያያዘ ሲነሱ የነበሩ የወሰን ማስከበር ችግሮች መፍትሄ ማግኘታቸው ና ግንባታው ከግማሽ በላይ መጠናቀቁም ነው የተገለጸው።
በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ መንገድ የብስክሌት መንገድንም ያካተተ መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!