Fana: At a Speed of Life!

በሳዑዲ የሚገኙ ድርጅቶች በወርቅ፣ ቴክኖሎጂና ማዳበሪያ ማምረት መሰማራት እንደሚፈልጉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ የመታብ አልነምር ኩባንያ (ማዕድን አውጪ) እና የአያድ አል አቶቢ ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ በወርቅ፣ ቴክኖሎጂና ማዳበሪያ ማምረት መሰማራት እንደሚፈልጉ ገለጹ፡፡

በሳዑዲ አረቢያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ የኩባንያዎቹን ባለቤትና ማኔጀሮችን በጽህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል።

በውይይቱም፥ በኢትዮጵያ ስላለው ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጭ፣ በስፋት ስለሚገኘው የፖታሽ፣ የወርቅና የተለያዩ ማዕድናት ክምችት ገለጻ አድርገዋል፡፡

ኩባንያዎቹ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎች እንዲሰማሩ ግብዣ መቅረቡም ነው የተነገረው።

ኩባንያዎቹ ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለፃ ያመሰገኑ ሲሆን፥ በወርቅ፣ በቴክኖሎጂና ማዳበሪያ ማምረት ዘርፍ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ በኢትዮጵያ ተገኝተው በእነዚህ መስኮች ላይ ጥናት በማድረግ ኢንቨስት እንደሚያደረጉ ቃል መግባታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.