Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ የፈጠራ ሐሳቦች ላደረሱ ወገኖች ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፈጠራ ሐሳቦች ላደረሱ ወገኖች ምስጋና አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በinnovation.covid19.et አማካኝነት መልካም የፈጠራ ሐሳቦች እየደረሷቸው መሆኑን በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል።

“አቅማችንን እና ትኩረታችንን ውጤታማ በሆኑ ተግባራት ላይ ማድረጋችን ኢትዮጵያን የማበልጸግ አንድ አካል” መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ፍሬያማ ሐሳቦችን በማፍለቅ እና ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን ጠንካራ እና ያደገች ሀገር እንገንባ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.