Fana: At a Speed of Life!

በጤፍ ምርት ላይ እሴት በመጨመር ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እሴት በመጨመር የጤፍ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል “አንድ ተመራጭ ምርት በአንድ ሀገር” የተሰኘ የሁለት ዓመት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ መንግስት እና የዓለም የእርሻና ምግብ ድርጅት ትብብር የተዘጋጀ ነው።

በኢትዮጵያ አመጋገብ ስርዓትን ለማሻሻል ጤፍን በልዩ ጥራት ማምረት የሚያስችል ፕሮጀክት መሆኑም ተገልጿል።

በጤፍ ምርት ላይ እሴት በመጨመር የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነም ተጠቁሟል።

ፕሮጀክቱ የዓለም እርሻና ምግብ ድርጅት በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2021 ጀምሮ ለአምስት ዓመት የሚቆየው የዓለም አቀፍ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የተመራጭ የግብርና ምርቶች ፕሮግራም አካል ነው።

የዓለም እርሻና ምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ፋራይ ዚሙዲዚ እንዳሉት፥ የተመራጭ የግብርና ምርቶች መርሀ ግብር አካል የሆነው የ”አንድ ተመራጭ ምርት በአንድ ሀገር” ፕሮጀክት የኢትዮጵያን ጤፍ ምርታማነት ለማሳደግ የጎላ ሚና አለው።

ጤፍ የፕሮጀክቱ አካል እንዲሆን በኢትዮጵያ መንግስት የተመረጠ መሆኑን ገልጸው፣ ጤፍ ከግሉቲን ነፃ በመሆኑ በመላው ዓለም ተፈላጊ ምርት እየሆነ መጥቷል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ጤፍ ሚሊየኖች አርሶ አደሮች የሚያመርቱትና የምግብ ዋስትናቸው መሰረት በመሆኑ ምርታማነቱን ማሻሻያ ለነገ የሚባል አይደለም ብለዋል።

ጤፍ በተለያየ የግብርና ስነ-ምህዳር የሚመረት አሁን ያለበትን በቂ ያልሆነ ምርታማነት ማሻሻያ ይገባናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በጤፍ ምርት ላይ እሴት በመጨመር የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሁሉንም አካላት ትብብር እንደሚጠይቅም ገልጸዋል።

የዓለም እርሻና ምግብ ድርጅት የአርሶ አደሩን የአመራረት ስልት በማሻሻል ቀጣይነት ያለው ምርታማነትንና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ዘርፍ አማካሪ አብዱልሰመድ አብዶ÷ በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሶስት ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በጤፍ ይሸፈናል ብለዋል።

ከ70 ሚሊየን በላይ አርሶ አደሮች የሚሳተፉበትና በስፋት የሚመረት መሆኑን ገልጸዋል።

የዓለምን 90 በመቶ ጤፍ የምታመርተው ኢትዮጵያ በአውሮፓ፣ አሜሪካና ኤዥያ ሀገራት ተፈላጊ ምርት ቢሆንም የማምረት አቅሟን ያክል እየተጠቀመችበት አይደለም ብለዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.