ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) በአፋር ክልል በትምህርት ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) በአፋር ክልል በትምህርት ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎችን ተዘዋውረው እየጎበኙ ነው።
በአሁኑ ወቅት በክልሉ ሠመራ ከተማ ውስጥ በትምህርት ዘርፉ የተከናወኑ ስራዎችን ተዘዋውረው እየተመለከቱ ይገኛሉ።
ችግኝ በመትከልም አረንጓዴ አሻራቸውን ማኖራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
በቀጣይ በክልሉ በትምህርት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን ከክልሉ አመራሮች ጋር በመሆን እንደሚገመግም ይጠበቃል።
በመረሐ-ግብሩ ላይ በክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አሚና ሴኮ፣ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አብዱ ሀሰን እንዲሁም የገጠር መሬት አስተዳደር እና አካባቢ ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ አህመድ ኢብራሂም ተገኝተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!