Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል-አቶ ደመቀ መኮንን

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ተወያይተዋል።

አቶ ደመቀ በዚሁ ወቅት ÷ ደቡብ ኮሪያ ኢትዮጵያን ቀዳሚ የልማት አጋር አድርጋ መምረጧ እንደሚያስመሰግን ገልጸው የሁለቱ ሀገራት ረጅም ታሪክ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰዋል።

በዛሬው ውይይታቸውም ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች እንዲሁም በጋራ ተጠቃሚነት ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል።

የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን በበኩላቸው÷ ሁለቱ ሀገራት የቆየ ግንኙት ያላቸው ሃገራት መሆናቸውን ገልፀው ኢትዮጵያ ተመራጭ የልማትና የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን ጠቁመዋል።

ደቡብ ኮሪያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የልማት ትብብር ለማጠናከር እየሰራች መሆኑንም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.